የፍሪጅ የፍተሻ መንገዶች
አንድን የንግድ ድርጅት (ካፌ፣ ሬስቶራንት ወይም ሆቴል) ስንከፍት ወይም ስናስፋፋ ከፍተኛ ወጪ ከሚጠይቁ ዕቃዎችመካከል የንግድ ፍሪጆች (Commercial Refrigerators/Freezers) በግንባር ቀደምትነት ይጠቀሳሉ። ያገለገለ ፍሪጅ መግዛት የካፒታል ወጪን በከፍተኛ ሁኔታ የሚቀንስ ቢሆንም፣አስፈላጊውን ፍተሻ ሳያደርጉ መግዛት ግን ላስፈላጊ የጥገና ወጪ እና ለምግብ ብልሽት ሊዳርግ ይችላል።
በዚህ ጽሁፍ፣ ያገለገለ የንግድ ፍሪጅ በሚገዙበት ጊዜ በዋናነት መፈተሽ የሚገቧቸውን ነገሮች እና እንዴት በቀላሉ መፈተሽ እንደሚችሉ እንመለከታለን።
1. የኮምፕረሰር (Compressor) እና የሙቀት ቅዝቃዜ ፍተሻ
ኮምፕረሰር የፍሪጅ ዋና ልብ ነው። እሱ ከተበላሸ ወይም አቅሙ ከተዳከመ ፍሪጁ ሙሉ በሙሉ ስራ ያቆማል ወይም በቂ ቅዝቃዜአይሰጥም።
2. የደጋፊ እና የአየር ዑደት (Evaporator Fan) ፍተሻ
በፍሪጅ ውስጥ ያለው አየር እኩል እንዲሰራጭ የሚያደርገውየውስጥ ፋን (Fan) ነው። ፋኑ ካልሰራ ፍሪጁ የተወሰነው ክፍል ብቻ ቀዝቅዞ ሌላው ክፍል ሊሞቅ ይችላል።
3. የኤሌክትሪክ መስመር እና የፍሪጅ ዲጂታል መቆጣጠሪያ (Thermostat)
ዘመናዊ የሆቴል ፍሪጆች የሙቀት መጠን ማሳያ (Digital Controller) አሏቸው።
ፓወር ሰጥተው ዲጂታል ስክሪኑ መስራቱን ያረጋግጡ። ከጥቂትሰከንዶች በኋላ ሪሌዩ «ጠቅ» የሚል ድምፅ በማውጣትየኮምፕረሰሩን መስመር ማብራቱን እና ሴንሰሩ የሙቀት ለውጥን ማንበቡን ማረጋገጥ አለብዎት።
ማጠቃለያ: መሠረታዊው የኮምፕረሰር፣ የኤሌክትሪክ እና የፋንፍተሻ ለሁሉም አንድ ዓይነት ሲሆን፤ ለዲስፕሌይ ፍሪጅ በመስታወቱ እና አየር የማሰራጨት አቅሙ ላይ፣ ለዲፕ ፍሪዘር ደግሞ ከፍተኛ ቅዝቃዜ (-18°C) መስጠቱ እና አየር አለማስገባቱ ላይ ተጨማሪ ትኩረት ማድረግ ያስፈልጋል።
